Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የተባበሩት መንግስታት ኢትዮጵያ በቀጣናው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት የሰላም ግንባታ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሒደት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ  ገልጸው÷የኢትዮጵያ ሕዝብ ምክክሩን በቅርበት እየተከታተለውና እየደገፈው እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡

በሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያ ድጋፍ እንደምታደርግ የገለጹት ሚኒስትሩ÷ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነታቸው በእጅጉ እየተሻሻለ መምጣቱንም አስረድተዋል፡፡

ሮዝማሪ ዲካርሎ በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥም ሆነ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለምታደርገው ጥረት የተባበሩት መንግስታት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ ጌደዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበር (ዶ/ር) ጋር በአፍሪካ ቀንድ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version