Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ረጅም ታሪክና ጥልቅ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸው፣ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጉብኝትም ይሄንን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል፡፡

በተለይም በማህበራዊ ጥበቃና አካታችነት፣ የሴቶችን መብትና የስርዓተ ፆታ እኩልነት፣ ሴቶች በሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ረገድ ያላቸው አስተዋፅዖ እና ሴቶችን በኢኮኖሚ ማብቃት ዙሪያ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

ሚኒስትሯ የሴት ልጅ ግርዛትንና ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን በመከላከል ዙሪያ እስካሁን እንደ ሀገር የተሰሩና በመሰራት ላይ ያሉ ሥራዎችን በሚመለከት ገለፃ ማድረጋቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version