Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ መካሔድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዐዔ በወልቂጤ ከተማ መካሔድ ጀምሯል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የክልሉን መንግሥት የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል፡፡

ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጉባዔ በተለያዩ ደንቦች ላይ ከተወያየ በኋላ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version