Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዩናይትድ ኪንግደም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ራይነር የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ::

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ እና ልዑካቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ባደረጉት ጉብኝት፤ የኢትዮጵያ የአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ፣ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል እና የተግባራዊ በረራ ማሰልጠኛ ምስለ በረራዎችን ተመልክተዋል።

እንዲሁም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር አባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘመናዊ አውሮፕላኖቹ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ሂትሮው፣ ለንደን ጋትዊክ እና ማንቼስተር ከተሞች 16 ሳምንታዊ በረራ በማድረግ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ትስስርን ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል።

Exit mobile version