Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ፖሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስምሪት እንዲሰፋ ይደረጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስምሪቱን እንዲያሰፋ ድጋፍ ይደረጋል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ እና የጸጥታና ደኅንነት ኃላፊ ጊልስ ሚቻውድ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከጊልስ ሚቻውድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም የተባበሩት መንግሥታት በኢትዮጵያ የሚያከናውናቸው ተልዕኮዎች እንዲሳኩ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ኮሚሽነር ጀኔራሉ አስረድተዋል፡፡

በቀጣይም ይህንኑ ተግባር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።

ምክትል ዋና ፀሐፊው በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ያላቸው ትብብር በአርያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል፡፡

የፖሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ስምሪትን ለማስፋት ለቀረበላቸው ጥያቄም ተቋማቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version