አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና ተከታታይ መርሐ-ግብር ሲያስተምራቸው የነበሩ ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ(ዶ/ር) ፥ ትምህርት የሁሉ ነገር ቁልፍ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ጊዜያት የሀገርን ሁለተናዊ ለውጥ የሚያስቀጥሉ ተማሪዎችን እያሰለጠነ ይገኛል ብለዋል ።
በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው በተሰጠው የትምህርት መስክ እና ተልዕኮ በምርምር እና በማህበረሰብ አገልግሎት የተጣለበትን ኃላፊነት ይወጣል ነው ያሉት ።
በተጨማሪም መቱ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ-ግብሮች ሲያስተምራቸውን የነበሩ 1 ሺህ 400 ተማሪዎችን በመጀመሪያና እና ሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል።
ከእነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 181 የሚሆኑት በመጀመሪያ ዲግሪ እና 226 የሚሆኑት ደግሞ በ2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።
በኢብራሂም ባዲ