Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በስንቅሌ የቆርኬዎች መጠለያ ለጎብኚዎች አገልገሎት የሚሰጥ ሎጅ ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በስንቅሌ የቆርኬዎች መጠለያ ለጎብኚዎች አገልገሎት የሚውል የማሕበረሰብ አቀፍ ሎጅ ክፍት መደረጉን ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሎጁ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው፤ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴዔታ ስለሺ ግርማ፣ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና የአካባቢው ማሕበረሰብ በተገኙበት ነው፡፡

የአገልግሎት ማዕከሉ የአሥተዳደር መመሪያም ለሚመለከታቸው የማሕበረሰቡ ተወካዮች ርክክብ መደረጉን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የዱር አእንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እና ፒ ኤች ኢ ሲ ኢ የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ትብብር ሎጁ ለአገልግሎት መብቃቱም ተገልጿል፡፡

Exit mobile version