አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና የከተማው ነዋሪዎች መሳተፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይት መድረኩ በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡