Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቻይና ቢዝነስ ልዑክ ቦሌ ለሚና ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ዓለም አቀፍ ንግድ ማስፋፊያ ም/ቤት ምክትል ሊቀመንበር የተመራ የቢዝነስ ልዑክ ቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎብኝቷል፡፡

ልዑካኑ በጉብኝታቸው በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቹ ስላለው መሰረተ ልማት፣ የባለሃብቶች ተሳትፎ እንዲሁም አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት የቻይና ባለሃብቶች ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የማስተዋወቅና የማግባባት ሥራዎችን እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና ገብተው ሥራ ከጀመሩ ባለሃብቶች መካከል የቻይና ባለሃብቶች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version