አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የእውቅና እና የታክስ ንቅናቄ መድረክ “ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።
መድረኩ ከገቢዎች ሚኒስቴር ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡