Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በስኬት መጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

በጨረታው 27 ባንኮች መሳተፋቸውን ባንኩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስፍሯል፡፡

በዚህም አማካይ የምንዛሪ ጨረታ ዋጋ አንድ የአሜሪካን ዶላር 135 ነጥብ 6185 ብር ሆኖ መመዘገቡን ነው ያስታወቀው፡፡

የውጭ ምንዛሪ የገበያ ሁኔታን በቅርበት በመከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ሽያጮችን እንደሚያካሂድም ጠቁሟል፡፡

Exit mobile version