አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አየርላንድ በኢትዮጵያ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ገለጸች፡፡
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ከአየርላንድ አምባሳደር ኦሊቪያ ሌስሊ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም አየርላንድ በኢትዮጵያ በማኅበራዊ ጥበቃና ሴቶችን በማብቃት ረገድ እያደረገችው ላለው ድጋፍ ሚኒስትሯ አመሥግነዋል፡፡
ይህ ትብብርም በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
አምባሳደሯ በበኩላቸው የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር፤ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ጥረት ሀገራቸው እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል፡፡