Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፎረም በደቡብ ኮሪያ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ200 በላይ የሚሆኑ የኩባንያ ባለቤቶች በተገኙበት የኢትዮጵያን እምቅ የኢንቨስትመንት እድል ለኢንቨስተሮች የሚያስተዋውቅ ፎረም በደቡብ ኮሪያ ሴዑል ተካሂዷል፡፡

በዝግጅቱ ላይ በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሴ ዳልኬ÷ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የተሻለ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ማበረታቻዎች እንዳላት አስገንዝበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት ምህዳር ለመፍጠር በመንግስት የተደረጉ ፖሊሲ ማሻሻያችን፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች እና ምቹ የንግድ ከባቢያዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለመድረኩ ተሳታፊዎች ገለጻ ተደርጓል።

የደቡብ ኮሪያ ባለሃብቶች በኢትየጵያ ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሳተፉ አምባሳደር ደሴ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የፎረሙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ ፎረሙ ኢትዮጵያ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ያላት ሀገር መሆኗን የተረዱበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማየት የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት ለማድረግ እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን በደቡብ ኮሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version