Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ የበልግ እርሻ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2017 በጀት ዓመት የበልግ እርሻ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በዲላ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን በትኩረት በማከናወን ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ እንደሆነ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version