አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 7ኛ መደበኛ ጉባዔውን ተጨማሪ በጀት፣ ዐዋጆችና ደንቦችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ፡፡
ምክር ቤቱ ለአንድ ቀን ባካሄደው ጉባዔ በክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ በቀረበው የ2017 በጀት ዓመት የሥድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከተወያየ በኋላ አጽድቋል፡፡
እንዲሁም በምክር ቤቱ የቀረበውን የ665 ሚሊየን 558 ሺህ 802 ብር ተጨማሪ በጀትን ማጽደቁ ተገልጿል፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የቀረቡለትን የተለያዩ ረቂቅ ዐዋጆችና ደንቦችን ማጽደቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

