አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀርቧል።
በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍስሃ ሻውል ከህንድ የንግድ ተቋማት ሥራ ሃላፊዎች እና ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ውቅት አምባሳደር ፍስሃ÷ ኢትዮጵያ ያሏትን የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ፀጋዎችን በተመለከተ ገለፃ አድርጎላቸዋል።
የህንድ ኢንቨስትመንት ተቋማት እና ባለሃብቶችም በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማሩ ጋብዟቸዋል፡፡