Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ለጅቡቲ-ኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን-ዩጋንዳ ኮሪደር ስምምነት ትግበራ ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጅቡቲ-ኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን-ዩጋንዳ ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ በትናንትናው ዕለት ተፈርሟል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ስምምነቱ ቀጣናዊ የንግድ ልውውጥን ለማሳደግና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጠናከር ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የኮሪደሩ ምስረታ የጋራ ብልጽግናን በሚያረጋግጥ አግባብ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆን ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

ሀገራቱ በቀጣናው የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴዎች የተሳለጡ እንዲሆኑ እና ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version