Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ክልሎች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎች 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል እየተከበረ ነው።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ በሚገኘው መርሐ ግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን (ዶ/ር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ የዓድዋ ድል በዓል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ፖሊስ አባላት እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

እለቱን በማስመልከት የዓድዋን ድል የሚዘክሩ ልዩ ልዩ የሙዚቃ ትርኢትና ዝግጅቶች እየቀረቡ ይገኛሉ።

Exit mobile version