Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂ ምዝገባ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡

በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ-አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር)፣ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር ዮዳሄ አርዓያስላሴ እና የአዲስ አበባ ት/ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የተማሪዎች የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በትብብር እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

በመርሐ ግብሩ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሆኑ ህጻናት የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የት/ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ መግለጹን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ መረጃ አመልክቷል፡፡

Exit mobile version