አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርባ ምንጭ ከተማ የተካሄደው 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል ብሔራዊ ትርክትን በሚያጠናክር መልኩ መከበሩን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
የበዓሉን አከባበር አፈፃፀም የሚገመግም መድረክ በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል፡፡
አፈ-ጉባዔው በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ በዓሉ ብሔራዊ ትርክትን በሚያጠናክር መልኩ መከበሩን አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ እየመከረች በምትገኝበት ጊዜ የተከበረ በዓል በመሆኑም ልዩ እንደሚያደረገው ጠቅሰዋል፡፡
የበዓሉ ዐቢይ ኮሚቴ ግምገማም የተገኙ ውጤቶችን በመለየት ለቀጣይ ዝግጅት ግብዓቶችን መውሰድ ነው ብለዋል፡፡
በበዓሉ አከባበር ላይ የላቀ አፈፃፀም ለነበራቸው አካላት የዕውቅና መርሐ-ግብር እንደሚኖርም ተገልጿል፡፡
በሰለሞን በየነ

