Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

41ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 41ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ “ገዢ ትርክት ለህብረ ብሔራዊ ሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እና ምሁራን ተገኝተዋል፡፡

አቶ ሃይሉ አዱኛ በዚህ ወቅት÷ ገዢ ትርክት ሀገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባለፈ ፈተናዎችን በድል ለመሻገር ያስችላል ብለዋል፡፡

ለአብነትም ከሁሉም አቅጣጫ የተነሱ ኢትዮጵያውያን በጋራ ባደረጉት ተጋድሎ ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል ሆኖ መመዝገቡን አውስተዋል፡፡

በመድረኩ የዓድዋ ድል ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በበሃይሉ ባኔ

Exit mobile version