Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ፌስቲቫል ሳምንት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ፌስቲቫል ሳምንት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ የባህል ፌስቲቫሉ ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

ባህሎቻችን በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው ለሀገር ግንባታ፣ ለህዝቦች መቀራረብና አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም ለሰላም እና ለወል ትርክት ግንባታ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ ሲሉም ገልጸዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች “ባህሎቻችን የወል ትርክት አምባ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደውን የባህል ፌስቲቫል በጊዮን ሆቴል በመገኘት እንዲጎበኙም ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Exit mobile version