Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያን የኢቨስትመንት ዕድሎች ለማስተዋወቅ እሠራለሁ- ጄትሮ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን የኢቨስትመንት ዕድሎች ለጃፓን ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ እንደሚሠራ የጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት (ጄትሮ) አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሐ ይታገሱ (ዶ/ር) ከጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት ካዙያ ናካጆ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዕድሎችና አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አብራርተዋል፡፡

የጃፓን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉም ድርጅቱ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱም በቀጣይ የኢትዮጵያን የኢቨስትመንት ዕድሎች ለጃፓን ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ በድርጅታቸው በኩል እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ የአዲስ አበባ ቢሮውን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡

በቀጣይ ከሚካሄደው “ቲካድ – 9” ጎን ለጎንም፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትና ቢዝነስ ዕድሎች የሚያስተዋውቅ መድረክ እንዲያዘጋጁ መጠየቃቸውን የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version