Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአጋም በር የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ ከ631 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የአጋም በር የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀምሯል።

ፕሮጅክቱ ሲጠናቀቅ በጣርማ በር ወረዳ የሚገኙ አራት ቀበሌዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ ግንባታው ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ነው የተገለጸው፡፡

የግንባታ ወጪው በዋን ዋሽ ፕሮግራም እንደሚሸፈን መጠቀሱን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version