Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሲዳማ ክልል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ “ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ሀሳብ የንቅናቄ መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በክልሉ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ ኢንዱስትሪዎችን የማስፋፋት እና ስራ ያቆሙ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ማሳደግ መቻሉ ተመላክቷል።

በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልል ደረጃ የኢንዱስትሪ ልማት ስራዎችን በማጠናከር በርካታ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂዎችን ለማሳደግ እንደሚረዳ ገልጸው፤ የመጡ ውጤቶችን የበለጠ በማጠናከር የኢንዱስትሪ ልማት ማነቆዎችን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት የሚመለከታቸው አካላት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳየ ጎዳና ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መጀመሩ የሀገር ዉስጥ ምርቶችን የመጠቀም ባህል ለማሳደግ፣ የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻልና የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚጠቅም መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version