Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የምክር ቤቶቹ አባላት ከሕዝቡ ጋር ያደረጉትን ውይይት አስመልክቶ ግብረ መልስ እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል እና የክልል ምክር ቤቶች አባላት ከሕዝቡ ጋር ያደረጉትን ውይይት አስመልክቶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት ግብረ መልስ እየሰጡ ነው።

የምክር ቤቶቹ አባላት በክልሉ በተለያዩ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከመራጩ ሕዝብ ጋር ላለፉት 15 ቀናት ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ፋጤ ስርሞሎ በመድረኩ እንደገለጹት፤ አባላቱ ከመራጩ ሕዝብ ጋር በሰላም፣ በልማት፣ በመልካም አሥተዳደር እና ከፕሮጀክት አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ተወያይተዋል፡፡

ከሕዝቡ ጋር የተደረገው ውይይት እና የመስክ ምልከታ ላይ የታየውን አፈጻጸም በተመለከተም ከዞን እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር ለሚመለከታቸው አካላት ግብረ መልስ ተሰጥቷል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በዛሬው ዕለት ደግሞ የምክር ቤቶቹ አባላት ከሕዝቡ ጋር የነበራቸውን ውይይት አስመልክቶ ለክልሉ መንግሥት ግብረ መልስ መስጠት የሚያስችል የውይይት መድረክ እያካሄዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

Exit mobile version