Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለአገልግሎቱ የአካል ድጋፍ ማምረቻ ግብዓቶችን ድጋፍ ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው የአካል ድጋፍ ማምረቻ ግብዓቶችን በድጋፍ አገኘ፡፡

ድጋፉን ያደረገው የጂዊሽ ጆይንት ዲስትሪቢዩሽን ግሪድ ኮሚቴ ነው፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት፤ ድጋፉ የአካል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ሰው ሠራሽ አካል ተደራሽ ለማድረግ ያግዛል፡፡

በተጨማሪም አካታች የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አብረሃም ንጉሴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሁለቱ ሀገራት በጤናው ዘርፍ በበርካታ የትብብር መስኮች በጋራ እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version