Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዱር እንስሳት ጥበቃ ላይ ያተኮረ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንድነት ፓርኮች ኮርፖሬሽን እና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በዱር እንስሳት ጥበቃ ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ታምራት ኃይሌ (ዶ/ር) እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በዚሁ መሠረት ስምምነቱ፤ በዱር እንስሳት ጥበቃ ዘርፍ፣ በትምህርት እና ስልጠና ዕድሎች፣ በጥናት እንዲሁም ምርምር ሥራዎች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የስምምነቱ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ የሚገኙ  እና ዝርያቸው የመጥፋት አደጋ ያንዣበበባቸው የዱር እንስሳትን  ማለትም፤ የኢትዮጵያ ተኩላ፣ የአፍሪካ ዝሆኖች እና የጫካ ፈረሶች  ላይ ጥናትና ምርምሮችን ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ የተጠቀሱትን እንስሳት ጤና ለመጠበቅ፣ የሚራቡበትን ሁኔታ ለመፍጠር፣ የመኖሪያ አካባቢያቸውን ለመጠበቅ እና የአመጋገብ ሁኔታቸውን ለመከታተል ያስችላል ነው የተባለው፡፡

በየሻምበል ምኅረት

Exit mobile version