አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የዘላቂ ልማት ግቦች የስትሪንግ ኮሚቴ ስብሰባ መካሄዱን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ስብሰባውን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ድጋፍ አስተባባሪ ራሚዝ አላክባሮቭ እንደመሩት ተገልጿል።
በስብሰባው ላይ ሚኒስትሮችና የልማት አጋሮች ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ የኢትዮጵያን የዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራ ለማፋጠን ወሳኝ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።