አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀጣዮቹ በቀጣዮቹ ቅዳሜ እና እሑድ በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ለሚካሄደው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር የካቲት 29 እና 30 ቀን 2017 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መርሐ ግብር ያካሂዳል፡፡
መርሐ ግብሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ የተወሰኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሠረት በሁለቱም ቀናት ከቀኑ 5:00 ሠዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቅ ድረስ፦
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
• ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ላይ)
• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ለገሃር መብራት)
• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ቴሌ ማቋረጫ ላይ)
• ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ )
• ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ)
• ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መታጠፊያ) ላይ የሚዘጋ ሲሆን÷ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።