አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ዋግ ኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ በአሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ የተገነባው ኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ተጠናቅቆ ርክክብ ተደርጓል፡፡
ትምህርት ቤቱ በ206 ሚሊየን ብር ወጪ መገንባቱ ነው የተገለጸው፡፡
የኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከርና ተወዳዳሪ ትውልድ ለመፍጠር በሁሉም ክልሎች የኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን ገንብቶ እያስረከበ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡
ይህም ወንድማማችነትን ከማጠናከር ባለፈ የጋራ ብልጽግናን ለማፋጠን እንደሚያስችል መጠቆሙን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡