Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጎፋ ዞን ተወላጆች ወንድማማችነት ማጠናከሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎፋ ዞን ተወላጆች አንድነት እና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌን (ዶ/ር) ጨምሮ የፌዴራል እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የጎፋ ዞን ተወላጆች በዞኑ ልማት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እና ድጋፍ ማጠናከር እንደለባቸው በመርሐ ግብሩ ተነስቷል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ የተዘጋጀው ሰነድ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዳግማዊ አየለ (ኢ/ር) ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት እንደሚገኝም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመልክቷል።

Exit mobile version