Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከተማ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

በሊጉ ከሶስት ተከታታይ ድል በኃላ ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት ያጠናቀቁት ቡናማዎቹ በ33 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በ21ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታን 5 ለ 2 ካሸነፉበት ጨዋታ መልስ አቻ ውጤት ያስመዘገቡት ሀዋሳ ከተማዎች ደግሞ በ20 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከስሑል ሽረ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

Exit mobile version