Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ1 ሺህ 446ኛው የሐጅና ዑምራ ጉዞ የምዝገባ ጊዜ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ1 ሺህ 446ኛው የሐጅና ዑምራ ጉዞ የምዝገባ ጊዜ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም መራዘሙን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የተራዘመው የምዝገባ ሒደት ከትናንት ጀምሮ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ነው የተገለጸው፡፡

ምዝገባው የተሰጠው የጊዜ ገደብ በቂ አለመሆኑ በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ መራዘሙ ተገልጿል፡፡

ቀኑ የተራዘመው ፍላጎት ያላቸው ሐጃጆችን ለማስተናገድ በማለም መሆኑን የጠቆመው ምክር ቤቱ ÷ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ በተሰጠው ጊዜ እንዲመዘገብ ጥሪ አቅርቧል።

በሚኪያስ ዓለሙ

Exit mobile version