Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም ድጋፏን እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ የልማት ዳይሬክተር ፖል ዋልተርስ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሀገራቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር እንዲሁም በሁለትዮሽ የገበያ ዕድሎች ዙሪያ መምከራቸውን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለንግድና ኢንቨስትመንት መጎልበት በትኩረት እየሰራች መሆኑን ገልጸው÷ለዘርፉ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን አስረድተዋል፡፡

ፓል ዋልተርስ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ለዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት እያደረገች ያለውን ዝግጅት አድንቀው፤ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም የምታደርገውን ድጋፍ እንደምታጠናክር አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version