አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የኩላሊት ንቅለ ተከላ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት 2009 ጀምሮ ለ172 ህሙማን አገልግሎቱን መስጠቱ ተገለጸ፡፡
በጤና ሚኒስቴር የሜዲካል አገልግሎት መሪ ሥራ አሥፈፃሚ ባለሙያ ሲስተር እመቤት ታረቀኝ እንዳሉት፤ ሆስፒታሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ በኩላሊት ንቅለ ተከላ ሕክምና ብቸኛ ማዕከል ነው፡፡
ማዕከሉ ሙሉ የሰው ኃይል ቢኖረውም፤ ያለበት የክፍል ጥበት እና የቁሳቁስ እጥረት በይበልጥ አገልግሎቱን ተደራሽ እንያደርግ ተግዳሮት ሆኖበታል ብለዋል፡፡
በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች መሰል አገልግሎቶችን የሚሰጡ ማዕከላትን ማስፋፋት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
በሰለሞን ይታየው