አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በተለያዩ ክልሎች 34 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል፡፡
ጽሕፈት ቤቱ 13 ሺህ የትምህርት መርጃ መጻሕፍት፣ 500 መጽሐፍ የተጫነባቸው ታብሌት ኮምፒውተሮች፣ 2 ሺህ 500 የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በተጨማሪም በትምህርት ቤቶቹ ለሚገኙ ክሊኒኮች የሚሆን መድሃኒትና የህክምና ቁሳቁስ ተደርጓል።
ጽሕፈት ቤቱ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ በመላ ሀገሪቱ ባስገነባቸው ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች የደንብ ልብስ፣ ቦርሳን ጨምሮ አልባሳትና ሌሎች ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።