አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 5ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የስራ ቡድን አባላት ስብሰባ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ መካሄድ ጀምሯል::
የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ ቡድን መሪ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ኢትዮጵያ ለዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ዝግጁ መሆኗን በመድረኩ አስረድቻለሁ ብለዋል፡፡
አባል ሀገራት የሁለትዮሽ የንግድ ድርድራቸውን ከወዲሁ እንዲያጠናቅቁ በመድረኩ ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጸው÷ በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ከ19 ሀገራት በላይ የድጋፍ መልእክት በማስተላለፍ ኢትዮጵያን ማበረታታቸውን ገልፀዋል፡፡
መድረኩ በጥያቄና መልስ መርሐ-ግብር እስከምሽት እንደሚቀጥልም አመላክተዋል፡፡