Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተሠሩ ስራዎችን ለዓለም ለማሳየት ያለመ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከግንቦት 8 ጀምሮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ኢት ኤክስ ኤክስፖ 2025 ከግንቦት 8 ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ኤክስፖውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ እንደሚያዘጋጁት ተመላክቷል።

ኤክስፖው የሳይበር ደህንነት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ፋይን ቴክ፣ ስማርት ሲቲ እና የቴክኖሎጂ ትምህርትን መሰረት ያደረገ አምስት የትኩረት መስኮችን የያዘ ነውም ተብሏል።

በቴክኖሎጂው ዘርፍ እንደ ሀገር የተሠሩ ስራዎችን ለዓለም ለማሳየት እና በቀጣይ መሰራት የሚገቡ ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ አቅምን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነም ተገልጿል።

የሦስት ቀናት ቆይታ በሚኖረው ኤክስፖው ላይ የኤአይ እና ሮቦቲክስ ውድድሮች፣ ዐውደ ርዕዮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ አቅምን የሚፈጥሩ በርካታ የጎንዮሽ ውይይቶች እንደሚደረጉም ተመላክቷል።

በዐውደርዕዩ ላይ 10 ሺህ እንግዶች ይታደማሉ ተብሎም ነው የሚጠበቀው።

በፍቅርተ ከበደ

Exit mobile version