Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሲዳማ ክልል የተገነባው ‘ኢፋ ቦሩ’ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል መንግስት ድጋፍ በሲዳማ ክልል ለኩ ከተማ የተገነባው ‘ኢፋ ቦሩ’ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል፡፡

በምረቃ ስነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በ149 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ትምህርት ቤቱ 18 የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ቤተ ሙከራና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችን የያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ከሰባት ወራት ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀዉ ትምህርት ቤቱ፤ በየዕለቱ ረጅም ርቀት በመጓዝ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በአካባቢዉ እንዲማሩ ያስችላቸዋል ተብሏል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎች መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተነግሯል።

Exit mobile version