አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ እንዲሁም አርሰናል ከብሬንትፎርድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ቀን 8 ሰዓት ከ30 በሚደረገው የሳምንቱ የመክፈቻ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን በሜዳው የሚያስተናግደበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
መርሐ ግብሩ ሲቀጥል ቀን 11 ሰዓት ላይ ሶስት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን÷በዚህም ብራይተን ከሌስተር ሲቲ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከኤቨርተን እንዲሁም ሳውዝሃምፕተን ከአስቶንቪላ ይገናኛሉ፡፡
በቅዳሜ ጨዋታዎች ማጠናቀቂያ ምሽት1 ሰዓት ከ30 ላይ አርሰናል በኤሚሬትስ ስታዲየም ብሬንትፎሮድን የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡

