አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳለጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ትናንት የተጀመረው የኢትዮ-ኬንያ የድንበር ላይ ንግድ ድርድር መቋጨቱን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት ከኬንያ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሊ ኪንያንጁ ጋር የትግበራ ስምምነት መፈራረማቸውን አመላክተዋል።
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት በሚያሳልጥ አግባብ የተፈረመ መሆኑን የገለጹት ካሳሁን (ዶ/ር)÷ በድንበር አካባቢ የሚገኙ ህዝቦች የመሰረታዊ የዕለት ፍጆታ ያለምንም የአቅርቦት ችግር እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነም ጠቁመዋል።