Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለትንሣኤ በዓል ያስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት

‹‹ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለእየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!!!

የትንሳኤ በዓል እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የሰው ልጆችን ከሃጢያት ለማንጻት ራሱን አሳልፎ በመሰጠት ወደር የማይገኝለት ፍቅሩን በመስቀል ላይ ገልፆ በሞቱ ለሰዉ ልጆች ሁሉ ምህረት ያስገኘበት እና ሞትንም ድል በመንሳት ከሞት የተነሳበት በዓል ነው።

እኛም እየሱስ ክርስቶስን በተምሳሌትነት በመከተል እርስ በርስ በመፋቀር፣ በመተሳሰብ፣ በይቅርታና ምህረት በማድረግ ከሰዉ ልጆች ጋር ሁሉ በሰላም እንድንኖር እሱ ይርዳን።

በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ፣ የምህረት፣ የመተሳሰብ፣ የመርዳዳት፣ የደስታ እና አብሮነታችን የሚጠናከርበት ይሁን።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፣ መልካም በዓል››

 

Exit mobile version