Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ማንቼስተር ሲቲ ኤቨርተንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ኤቨርተንን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የማንቼስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኦ-ሬልይ እና ኮቫቺች ማስቆጠር ችለዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ በ58 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ኤቨርተን በ38 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር፤ ብሬንትፎርድ በሜዳው ብራይተንን አስተናግዶ 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የብሬንትፎርድን የማሸነፊያ ግቦች ምቤሞ (2) ዊሳ እና ኖርጋርድ ሲያስቆጥሩ፤ ለብራይተን ደግሞ ዳኒ ዌልቤክ እና ሚቶማ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ዌስትሀም ዩናይትድ በሜዳው አስቀድሞ መውረዱን ካረጋገጠው ሳውዝሃምፕተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ሲያጠናቅቅ፤ ክሪስታል ፓላስ እና ቦርንመዝ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ 0 ለ 0 ተጠናቅቋል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ሲቀጥል አስቶን ቪላ ከኒውካስል ዩናይትድ በቪላ ፓርክ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

Exit mobile version