አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት በጀርመን በተካሄደው የአዲዳስ አዲዜሮ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅተዋል።
በ5 ኪሎ ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ ስታሸንፍ÷ በወንዶቹ ዮሚፍ ቀጀልቻ በቀዳሚነት አጠናቀዋል።
ከፍተኛ ፉክክር በተደረገበት የሴቶች 5 ኪሎ ሜትር ውድድር የሁለት ዓመታት አሸናፊዋ አትሌት መዲና ኢሳ በቀዳሚነት አጠናቃለች።
አትሌት ፎትየን ተስፋይ የሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ÷ አትሌት ገላ ሀምበሴ በሦስተኛነት ማጠናቀቅ ችላለች።
እንዲሁም በወንዶች የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ አንደኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።
በሴቶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ደግሞ ፋንታዬ በላይነህ በሁለተኛነት ስታጠናቅቅ÷ አትሌት ሰናይት ጌታቸው፣ አትሌት ግርማዊት ገብረእግዜር፣ ዓለምአዲስ እያዩ እና አትሌት ለምለም ንብረት በተከታታይ ከሦስተኛ እስከ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በተመሳሳይ በወንዶች የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ገመቹ ዲዳ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ መቻሉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል።