አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ወደ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡
ወላይታ ድቻ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገውን ሸገር ከተማን ባሸነፈበት ጨዋታ ዘላለም አባተ እና ብዙዓየሁ ሰይፈ የማሸነፊያ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡
ወላይታ ድቻ ድሉን ተከትሎ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታቸውን ከሚያደርጉት መቻልና ሲዳማ ቡና አሸናፊ ጋር በፍጻሜው ይፋለማል፡፡
በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚ የነበረው ወላይታ ድቻ በፍጻሜው በኢትዮጵያ ቡና ተሸንፎ ዋንጫውን ማጣቱ ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን የሚሆነው ክለብ በቀጣዩ ዓመት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ ተሳታፊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡