Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ፖሊስ በምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት የስፖርት ውድድር በጦር ውርወራ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛው የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት የስፖርት ውድድር የኢትዮጵያ ፖሊስ በሴቶች የጦር ውርወራ የፍጻሜ ውድድር 1ኛ እና 2ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆኗል።

በውድድሩ የኬኒያ ፖሊስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

በወንዶች ጦር ወርወራ የኬኒያ ፖሊስ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ የኢትዮጵያ ፖሊስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።

የኬኒያ ፖሊስ በ200 ሜትር ሩጫ በሴቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት ሲያሸንፉ÷ በወንዶች የኬኒያ ፖሊስ 1ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስም በወንዶች 200 ሜትር ሩጫ 2ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቋል፡፡

በአጠቃላይ ከተዘጋጀው 12 ሜዳሊያ መካከል የኬኒያ ፖሊስ 8 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሲመራ÷ የኢትዮጵያ ፖሊስ 4 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የፀጥታና ጥበቃ ዋና መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር አበራ ሁንዴ እና የደቡብ ሱዳን ፖሊስ ተወካይ ሌተናል ጄኔራል ቤንጃሚን ጆን ባቲስት ለአሸናፊ አትሌቶች ሜዳሊያ ሰጥተዋል።

Exit mobile version