Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የወጪ ጭነት 14 በመቶ ማደጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የወጪ ጭነት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 14 በመቶ ማደጉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታ ደንጌ ቦሩ ገለጹ፡፡

እያደገ የመጣውን የወጪ እና ገቢ ጭነት ከማሳለጥ አኳያ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰው፤ ይህን ተከትሎም በሎጂስቲክስ ዘርፉ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡

ለአብነትም በአንድ ወር ውስጥ እስከ 40 ሺህ ቶን ቡና በኮንቴይነር እንዲጓጓዝ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ የተለየ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ይህ ተግባር እንዲሳለጥ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የተለያዩ የቁም እንስሣትን ጨምሮ አትክልትና ፍራፍሬም በባቡር ወደ ውጭ እየተጓጓዘ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ከሀገሪቱ የወጪ ገቢ ጭነት ውስጥ 13 በመቶ በባቡር እንደሚጓጓዝ የገለጹት ሚኒስትር ዴዔታው፤ በቀጣይ የባቡር ድርሻን ለማሳደግ የሚያስችሉ የሪፎርም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

Exit mobile version