Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፋይዳ ለኢትዮጵያ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የፊታችን እሑድ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋይዳ ለኢትዮጵያ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ እንደሚካሄድ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

የጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዩዳሔ አርአያስላሴ በሰጡት መግለጫ÷ፋይዳ መታወቂያ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

እስካሁን ድረስም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ15 ሚሊየን በላይ ዜጎች ለፋይዳ መታወቂያ መመዝገባቸውን ነው የገለጹት፡፡

የሩጫ ውድድሩ የፋይዳ መታወቂያን አስፈላጊነት ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።

መነሻውን እና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደርገው የሩጫ ውድድሩ የፊታችን እሑድ ከጧቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በሩጫ ውድድሩ ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉም የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ለፋና ዲጂታል አስታውቋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version