Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሩሲያ የናዚ ኃይልን ያሸነፈችበት 80ኛ ዓመት የድል በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ ኃይል ወረራን በመመከት ያሸነፈችበት 80ኛ ዓመት የድል በዓል በመዲናዋ ሞስኮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡

የድል በዓሉ በሞስኮ አደባባዮች በተለያዩ ወታደራዊ ስነ ስርዓቶች እንዲሁም የጦርነቱ ሰማዕታትን በማሰብ መከበር ጀምሯል፡፡

በሺዎች የሚቆጥሩ ወታደሮች እንዲሁም ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች በአደባባይ ወታደራዊ ሰልፍ ያደርጋሉ፡፡

በተጨማሪም ሩሲያውያን ሀገራቸው በሶስት አውደ ውጊያዎች ናዚን ድል ባደረገችበት ወቅት የተሰው ዘመዶቻቸውን ፎቶ ግራፍ በመያዝ ወደ አደባባይ ወጥተው ሰማዕትነታቸውን ይዘክራሉ፡፡

Exit mobile version